በትምህርት ስኬታማነትን የሚያጎናጽፉ መርሆች

About The Book

በትምህርት ስኬታማነትን የሚያጎናጽፉ መርሆች (Principles for Successful Education) የተሰኘው መጽሐፍ ተማሪዎችን ለመርዳትና በውጤታቸው እንዲበለጽጉ ታስቦ የተጻፈ መጽሐፍ ነው። በዚህ መጽሐፍ ውስጥ የተዳሰሱ እጅግ ብዙ ርእሰ ጉዳዮች አሉ። እነዚህ የተዳሰሱ ርእሰ ጉዳዮች ሁሉ ውጤታማ ተማሪን ለመገንባት አስተዋጽኦ የሚያደርጉ ናቸው። ተማሪዎች ስለ ራሳቸውና ስለ ትምህርት እንዲሁም በዙሪያቸው ስላለው ነገር የአመለካከታቸው መለወጥ ለውጤታማነታቸው ከፍተኛውን ድርሻ የሚይዝ ስለ ሆነ፣ በዚህ በኩል መጽሐፉ ትኩረት አድርጓል። ስለ ራሳቸው ካላቸው ዝቅተኛ አመለካከት የተነሣ፣ መቼም ቢሆን በትምህርታቸው ሊሳካላቸው እንደማይችል አድርገው ራሳቸውን የሚቆጥሩ፣ ያለመሳካታቸው ምክንያት ምን እንደ ሆነ እንዲያውቁና ለበለጠ ውጤት እንዴት መነሣሣት እንደሚችሉ ለማሳየት ሕይወታቸውን ከውድቀት ወደ ስኬት ምዕራፍ የለወጡ ሰዎችን ሕይወት በመጠኑ ለመቃኘት ተሞክሯል። </p> በዚህ መጽሐፍ ውስጥ ተማሪዎችና ትምህርታቸውን የተመለከተ ጉዳይ ብቻ ሳይሆን፣ ሰፋ ያሉ ሌሎች የሕይወት ገጽታዎችም ተዳሰዋል። ተማሪዎች ምንም ዓይነት አዕምሮአዊ ዝግጅት ሳያደርጉ ወደ ተቃራኒ ጾታ መሳሳብ ውስጥ በመግባት ሕይወታቸው ለአደጋ እንዳይጋለጥ በቂ ሥነ ልቦናዊ ዝግጅት የሚሰጣቸው የሥነ ልቦና ሳይንስን እና የሰውን መንፈሳዊ ማንነት መሠረት ያደረጉ ሐሳቦችና ምክሮች ቀርበዋል። እንዲሁም፣ ተማሪዎች ሕይወታቸው በደስታና በታላቅ ስኬት የተሞላ እንዲሆን ስለ ዓላማ ያላቸውን ግንዛቤ የሚኮተኩት ጥናታዊ ጽሑፍም በመጨረሻው ምዕራፍ ላይ ቀርቧል። ትርፋማ ሕይወትን ለመኖር ከአሁኑ መዘጋጀት እንዳለባቸው የሚያምኑ ሁሉ መጽሐፉን ማንበብ አለባቸው እላለሁ። ይህ መጽሐፍ በዋነኝነት ለተማሪዎች ተብሎ የተዘጋጀ ቢሆንም፣ በልዩ ልዩ የሥራ መስክ ያሉ ሰዎች፣ ወላጆች፣ አስተማሪዎች ወ.ዘ.ተ ቢያነቡት ሕይወታቸውን ከውድቀት ወደ ስኬት እንዴት መለወጥ እንደሚችሉ ጥበብን ያገኙበታል። </p>
Piracy-free
Piracy-free
Assured Quality
Assured Quality
Secure Transactions
Secure Transactions
Delivery Options
Please enter pincode to check delivery time.
*COD & Shipping Charges may apply on certain items.
Review final details at checkout.
downArrow

Details


LOOKING TO PLACE A BULK ORDER?CLICK HERE