መመለስና መታደስ


LOOKING TO PLACE A BULK ORDER?CLICK HERE

Piracy-free
Piracy-free
Assured Quality
Assured Quality
Secure Transactions
Secure Transactions
Fast Delivery
Fast Delivery
Sustainably Printed
Sustainably Printed
Delivery Options
Please enter pincode to check delivery time.
*COD & Shipping Charges may apply on certain items.
Review final details at checkout.

About The Book

አሁን ባለንበት ዘመን እግዚአብሔር ምን እያደረገ ነው? በመጪዎቹ ዘመናትስ ምን ሊያደርግ ወስኖአል? እግዚአብሔር ሐሳቡን የገለጠውና እየገለጠ ያለው በቃሉ ነው። ወደ ቃሉ በቀረብን ቁጥር ሐሳቡ ግልጽ እየሆነልን ይመጣል። በእርግጥ ወደ ቃሉ መቅረብ ብቻ ሳይሆን በተዋረደና በሚፈልግ ልብ መቅረባችን ነው ሐሳቡ እንዳይሰወርብን የሚያደርገው።አንዳንድ ጊዜ የምንጠይቃቸው መንፈሳዊ ጥያቄዎች ቀጥተኛና ቀላል መልስ አይደለም ያላቸው። አንዳንድ ጊዜ ቀላል መልስ ያለው የሚመስለን የጥያቄውን ይዘትና መሠረት በሚገባ አለመረዳታችን ነው። እግዚአብሔር አሁን ባለንበት ዘመን እያደረገ ያለውን ለማወቅ ከቀደመው ዘመን ጀምሮ ምን እያደረገ እንደነበር መገንዘብ ያስፈልጋል። ስለዚህ እያደረገ ያለውን ለማወቅ ሲያደርግ የነበረውን ማስተዋል ቀዳሚ ነው። ምክንያቱም እግዚአብሔር አሁን የሚጀምረው ሥራ የለውም፤ ሥራው እየቀጠለ አሁን ያለንበት ዘመን ጋር ደርሷልና። እግዚአብሔር ሲያደርግ የነበረውን በሚገባ አጢነን ካላወቅን ሲያደርግ የነበረውን አሁን እያደረገ ይመስለናል። የሥራውን ቀጣይነት ካልተገነዘብን የተደረገውን ሳናውቅ የሚደረገውን ማወቅ የምንችል ይመስለንና በአዕምሮአችንና በእውቀታችን ውስንነት እንታለላለን።እግዚአብሔር ግን የነበረና ያለ፣ ደግሞም የሚኖር ነው። ማንነቱም ሆነ ሥራው በዚህ የጊዜ ማዕቀፍ ውስጥ ሊታይ ይገባል። አሁን ያለንበት ዘመን ግራ የምንጋባበትና እንደ እውር በጨለማ የምንዳክርበት አይደለም። የቃሉ ብርሃን የሚፈነጥቀው ብርሃን የመጣንበትንና ያለንበትን ብቻ ሳይሆን የምንሄድበትንም ያሳየናል። የመጣንበትን ካላወቅን፣ ያለንበትን ልናውቅ አንችልም። ያለንበትን ካላወቅን ደግሞ የምንደርስበትን ልናውቅ አንችልም። የቃሉ ብርሃን ጮራ ትላንትናና ዛሬ ላይ፣ እንዲሁም ነገ ላይ ያበራል። የዚያን ጊዜ የመጣንበትን ስለምናይ ኑሮአችንም ሆነ ዘመናችን ድንገተኛ አይሆንብንም፤ ከዚህ የተነሳ ባለንበት ግራ ሳንጋባ ያለንበት የበለጠ ትርጉም የሚሰጠን ይሆንልናል። ያለንበት ምክንያትና መነሻ እንዳለው ስለምናይ በዕይታም ሆነ በተስፋ እንሞላለን፤ ይህም ደግሞ የምንደርስበትን በማሳየት ውስጣችን ጉጉት ይፈጥራል። ስለዚህ በዚህ መጽሐፍ የመጣንበትን ካለማወቅ ከሚመጣ ድንገተኛነት፣ ወይም ያለንበትን ካለማወቅ ከሚመጣ ግራ መጋባትና የምንደርስበትንም ካለማወቅ ጉጉት የለሽ እንዳንሆን የሚያደርጉ የእግዚአብሔር ቃል ሐሳቦችና ዕይታዎች ተንጸባርቀዋል።
downArrow

Details