ኤርትሮ - ኢትዮጵያ

About The Book

ይህ መጽሓፍ፥ በኣንድ በኩል የኢትዮጵያ ህዝብና መንግስት ከምዕራባዉያን በተለይ ከተባበሩት መንግስታት ኣሜሪካ ልኣላውነቱን የሚጋፋ ተጽእኖ በሚወርድበት ባለው ባሁኑ ሰኣት፥ በሌላ በኩል ደግሞ የኤርትራ ህዝብ ላለፉት 20 ዓመታት በተባበሩት መንግስታት ኣሜሪካና ምዕራባውያን ኣገሮች ይወርድበት የነበረውን ጫናና ፍትሃዊ ያልሆነ የጸጥታው ምክር ቤትን ማዕቀብ 1907/2009 ተቛቑሞ ልኣላውነቱንና ነጻነቱን በማያወላውል መንገድ ማረጋገጡን፥ የኢትዮጵያ ህዝብ፥ በተለይ ሊሂቃኑ ተገንዝበው በኣርኣያነት በሚጠቕሱበት ባሉት ባሁኑ ወቅት ለኣንባብያን መቅረቡ፥ ኢትዮጵያውያን በኤርትራ ህዝብና መንግስት ላይ ኣዳብሮውት ባሉት ኣዎንታዊ ንቃተ ህሊና ትንሽ ድርሻ ይኖረዋል ብየ ኣምናሎህ።
ይህን መጽሓፍ፥ የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ኣመራር በኤርትራ ህዝብ የትግል ሂደት ውስጥ ጣልቃ በመግባት ይጠነስሳቸው የነበሩትን ሴራዎችና ያለ ኣቅሙ ይፈጽማቸው የነበሩትን ትንኮሳዎች፥ ህዝባዊ ግንባር፥ በልቦናና በሆደ ሰፊነት ችሎ ባካሄደው ከባድ ጦርነት ነጻነቱን ከመጉናጸፉ ባሻገር፥ ከፍተኛ መስዋእትነት በመክፈል የኢትዮጵያን ህዝብ ከደርግ ጨቋኝ ስርዓት ነጻ በማውጣት ወሳኝና የኣንበሳ ድርሻ ያበረከተ መሆኑን የሚያጉላ ነአ። ስለ ሆነም፥ በሁለቱም ኣገራት መካከል ለ30 ዓመታት የዘለቀው ጦርነት፥ በኤርትራ ህዝብ ላይ ብቻ ሳይሆን በኢትዮጵያ ህዝብ ላይም ከፍተኛ የሰው እልቂትና የንብረት ውድመት ያስከተለና ታሪኩም በመስተ-ጋብር የተሳሰረ ስለሆነ፥ የኢትዮጵያ ህዝብ ሊያውቀው ይገባል ከሚል እምነት፥ “ ኤርትሮ - ኢትዮጵያ፥ ከመጋረጃው በስተጀርባ” በሚል ርእስ መጽሓፉን ወደ ኣማርኛ ተርጉሜዋሎህ።
ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ፥ ከምስረታው ጀምሮ፥ ”ለኤርትራ ነጻነት ዘብ የቆምኩና የተከራከርኩ ነኝ” በማለት፥ የኤርትራውያንን ቀልብ ለማማለል ብዙ ጥሯል። በተለይ ከ 1998 በኋላ፥ በርካታ ኢትዮጵያውያን ይህን ኣባባል ኣምነውት ነበር። ኤርትራ ነጻነቷን ከተጎናጸፈች ከ27 ዓመታት በኋላም ቢሆን፥ ያገሪቱ ምሁራንና ፖለቲከኞች፥ “ወያኔ ከኤርትራውያን ባላነሰ ለኤርትራ ነጻነት ተሟግቷል” ብለው ጽፍዋል፥ ገናም እየጻፉ ናቸው።
ኣንዳርጋቸው ጽጌ፥ በኤርትራ ነጻነት ላይ የማያወላውል ኣቋም እንዳለው በተለያዩ ኣጋጣሚዎች ይገልጽ እንደነበር ባይካድም፥ በነሓሰ ወር 2018 “ያ ረፈረንደም፥ ወያነ ባስቸኳይ በኣንድ ዓመት ውስጥ እንዲካሄድ ባያደርግ ኖሮ፥ የ 5 ዓመት (ጊዜ) gap ኣግኝቶ ቢሆን ኖሮ፥ Normalize በሆነ ሁኔታ ውስጥ ተፈጥሮ ቢሆን ኖሮ፥ የኤርትራ ህዝብ ከኢትዮጵያ ህዝብ ጋር ካለው ኣጠቃላይ የሆነ ትስስር እንዲህ በቀላሉ 99% የሚሆን ህዝብ ነጻነት ብሎ የማይመረጥበት ሁኔታ ይኖር ነበረ . . .” ይልና፥ በ 2019 ኣጋማሽ ላይም፥ “ትውልድ እንዳይደናገር እኛም እንናገር” በሚለው መጽሓፉ፥ “የባህር በር ጉዳይ ኣንድ እልባት ካላገኘ የግዜ ጉዳይ ብቻ እንጂ ኣካባቢውን ለሌላ ቀውስ እንደሚዳርገው ከመቶ ፐርሰንት በላይ ርግጠኛ ሆኖ መናገር ይቻላል። ኢትዮጵያን የሚያህል ታሪካዊ ኣገር ማንም ቅኝ ገዥ ጠፍጥፎ በሰራቸው ሃገሮች ከባህር በር በቅርብ ርቀት እንዳትደርስ ተደርጋ የታሰርችበትን ገነድ ለመበጠስ የተለያዩ እርምጃዎች የሚወስድ ትውልድ መምጣቱ ኣይቀርም። ተስፋችን እነዚህ እርምጃዎች የሁለቱን ሃገር ድሃ ህዝቦች ለሌላ ዙር እልቂት የማይዳርጉ ይሆናሉ የሚል ነው።“ ሲል ከለውጡ በፊት ከነበረው ኣቋም ጋር የሚጣረስ ንግግር ሲናገር ተሰምቷል። እሱ ብቻ ሳይሆን፥ ኤርምያስ ለገሰም በኤርትራ ላይ ኣሉታዊ ኣቋም ነበረው የሚባል ባይሆንም፥ “. . . የኢትዮጵያ ህዝብ ብዛት 100 ሚልዮን ነው፥ ብያብር ኖሮ ኤርትራን ኣንድም ቀን ኣያቆያትም ነበር።” በማለት ኣፍራሽ ንግግር ማስደመጡ ግራ የሚያጋባ ነው። ቢያንስ ሁለቱም የኤርትራን ህዝብ ኣሳምረው ያውቁታልና።
ጀነራል ጻድቃን ገብረትንሳኤ በ 2020፥ “ …’ከኤርትራ ነጻነት በኋላ፥ የባህር-በር የሌላት ኢትዮጵያ ሃይል የሌላት መሆኗን ስለተገነዘብን፥ ተዋግተን ዓሰብን መያዝ ኣለብን ያልኩት እኔ ነኝ።” በማለት፥ የባህር-በር ማግኘት የሚል ኣዲስ የሚመስል ዲስኩር ማሰማቱ ላይ ቀደም ሲልም፥ በ (ግንቦት) 2000 ተቀዳ ኣለሙ፥ “ . . . በቅርብ ቀን ኣስደሳች ዜና ትሰማላችሁ። ዓሰብን እንይዛታለን ” ማለቱ ሲታከልበት፥ የፖለቲካ ተቃዋሚዎችና ምሁራን ድግሞ “ወያኔ የባህር በር ያስመልስልናል” ከሚል እሳቤ በመነሳት ተቃውሟቸውን እርግፍ ኣድርገው በመተው በ 1998 ጦርነት ወቅት፥ ህወሓትን በመደገፍ ሁለንተናዊ ማለት የገንዘብ የቁሳቁስና ሌሎች እርዳታዎች ማድረጋቸው፥ ከፍተኛ ፖለቲካዊ ድጋፍና ዲፕሎማስያዊ ቅስቀሳ ማካሄዳቸው የጠብ-ኣጫሪነታቸው መታያና ተቀጥያ እንደነበር መዘንጋት የለበትም።

የባህር በር የሚለውን ኣስተሳሰብ ኣሁንም ኣላባራም። ጠቅላይ ሚኒስተር ኣብይ ኣሕመድም ቢሆንም ከኣማራና ኦሮሞ ህዝብ ጦርነት ውስጥ ተዘፍቆ ባለበት ባሁኑ ሰዓት፥ የኤርትራን ልኣላውነት በሚጋፋ መልክ ከተጠቃሚነት ባሻግር የባህር በር ያስፈልገናል በማለት የኢትዮጵያ ህዝብ ከጎረቤት ኣገሮች በተለይ ከኤርትራና ጁቡቲ ህዝብ ጋር ወደ ጦርነት ለማግባት ዕረፍት ተስኖታትል።
በጥቅሉ ይህ መጽሓፍ፥
በኤርትራንና ኢትዮጵያ ኣዲስ የሰላም ምዕራፍ በተከፈተበት ባሁኑ ወቅት፥ ኢትዮጵያውያን የታሪክ ተመራማሪዎች፥ ፖለቲከኞችና ምሁራን ጦርነት ያስከተለውን ውድመት ተገንዝበው፥ ተጨባጭና እርግጠኛ በሆነ ታሪክ ዙርያ እንዲያስቡ፥ እንዲሁም፥
በተከታታይ የኢትዮጵያ ስርዓቶች የተከተሉት የተሳሳተ የጦርነት ፖሊሲ ሳቢያ፥ በቅድመና ድህረ ነጻነት በኤርትራ ላይ በተካሄዱት ሁለቱም ጦርነቶች (በተለይ በህወሓት ዘመን) በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን የመቅሰፍትና የኣካል-ጉዳተኝነት ሰለባ መሆናቸውን እንዲገነዘቡ ያደርጋል።

Piracy-free
Piracy-free
Assured Quality
Assured Quality
Secure Transactions
Secure Transactions
Delivery Options
Please enter pincode to check delivery time.
*COD & Shipping Charges may apply on certain items.
Review final details at checkout.
downArrow

Details

LOOKING TO PLACE A BULK ORDER?CLICK HERE