ጥሎ ማለፍ: Historical Novel (Amharic Edition)


LOOKING TO PLACE A BULK ORDER?CLICK HERE

Piracy-free
Piracy-free
Assured Quality
Assured Quality
Secure Transactions
Secure Transactions
Fast Delivery
Fast Delivery
Sustainably Printed
Sustainably Printed
Delivery Options
Please enter pincode to check delivery time.
*COD & Shipping Charges may apply on certain items.
Review final details at checkout.

About The Book

ይህ የሥነ-ጽሁፍ ሥራ በታሪካዊ ልቦለድነቱ ለአንባቢያን ቀርቧል፡፡ በታሪካዊ ልቦለድ አፃፃፍ ወግም አስፈላጊው ትኩረት እንዳይነፈገው ጥረት ተደርጓል፡፡ የተወሰነ ዘመንን ተንተርሷል፤ ከደርግ አሥራ ሰባት ያገዛዝ ዘመን. አሥራ አራቱን፡፡ የዘመነ ደርግን ምሥጢራዊ ሰነዶችና መዛግብቶችን፤ ከተነሳበት ጭብጥ አኳያ ፈትሿል፡፡ በዚህም ጠቃሚ መረጃዎችን ለታሪካዊነቱ ዋቢ አድርጓል፡፡ "ታሪካዊ ልቦለድ በኃላፊ ጊዜ ቢጋር ውስጥ ተቀንብቦ ከባለታሪኮቹና ከመረጃዎች ጋር ቁርኝት ቢኖረውም፤ የዘመኑን ትንሣኤና ውድቀት አበክሮ ከማውሳት አያልፍም'' የሚለውን የብዕሩን ሰው የአንቶኒ ትሮሎኘን ነቢብ መደላድሉ አድርጓል፡፡ ከእንግሊዛዊው የታሪካዊ ልቦለድ ደራሲና ገጣሚ ከሮበርት ግሬቭ የግል አስተያየት ጋርም ደራሲው የሚስማማበት ነጥብ አለው፡፡ ግሬቭ፤ "እራሴን ወደ ቀድሞ ዘመንና ትዝታዎች የመመለስ ስጦታው አለኝ፡፡ በዚህም ትናንት ምንና እንዴት እንደነበር ማየት እችላለሁ፡፡ ታሪካዊ ልቦለድም መጻፍ ያለበት በዚህ መልክ ነው፡፡'' ይላል፡፡ ይህ ታሪካዊ ልቦለድ ባንድ የደርግ ቋሚ ኮሚቴ አባል በነበረ ግለሰብ ሕይወት ዙሪያ የተጠነጠነ ነው፡፡ የግለሰቡን መነሻና መድረሻ፣ ከደርግ ሥልጣነ ዘመን ቆይታ ጋር ይመለከታል፡፡ በአብዮቱ ዘመን ውጣ ውረድ ውስጥ ያብዮተኞች እጣ ፈንታና መጨረሻ ምን እንደነበር በመረጃዎች ተደግፎ በታሪካዊ ልቦለድ አፃፃፍ ጥበብ አኳያ ለመቃኘት ተሞክሯል፡፡ ሥልጣን ያሰከራቸው ለማንም ለምንም እንደማይመለሱ ተስተውሏል፡፡ አንድ ዕውቅ ያገራችን ባለቅኔም፤'አንቺ የሥልጣን ፅዋ፣ ሲይዙሽ በተራገፈታሽ ጣፋጭ ነው፣ ጭላጭሽ መራራ፤ይኸንን እያየ፣ የሚተውሽ የለምይጋደልብሻል፤ የሰው ልጅ ዘላለም፤' ሲሉም የባለጊዜዎችንና የመንበራቸውን ፍጻሜ ያመለከቱት ሳይጠቀስ አይታለፍም፡፡
downArrow

Details