Jehovah Nessi

About The Book

<p>ያህዌ ንሲ - በዓላማ መኖርሰዎች ለባንዲራዬ እሞታለሁ ሲሉ፣ ለጨርቁ ማለታቸው አይደለም፤ በዚያ ሰንደቅ ለተወከለው ታሪክ፣ እሴት፣ ባህል፣ ግዛት (territory)ና ዓላማ ማለታቸው ነው። በዚያ ባንዲራ ውስጥ ብዙ ነገር ያያሉ። ከራሳቸው የሚሰፋና የሚተልቅ ነገር ያያሉ። ሙሴ እንደ ሰንደቅ ዓላማ በትሩን ከፍ ካደረገ በኋላና አማሌቅን ካሸነፈ በኋላ እግዚአብሔር ዓላማዬ ነው (ያህዌ ንሲ) የሚል መሠዊያ ሠራ። ለእግዚአብሔር ሕዝብ የድል መሠረት የሆነውን ነገር በዚህ መሠዊያ አሠመረበት። ከግብጽ የወጡ እስራኤላውያን ከራሳቸው የሚሰፋና የሚበልጥ ነገር ማየት ካልቻሉ፣ እግዚአብሔር ወዳሰበው ነገር ለመድረስና የሚፈልገውን ለመሆን ይቸገራሉ። ሰንደቅን የሚያይ ከራሱ የሰፋንና የተለቀን ነገር ማየት ይችላል። ያም ራሱን ሳይሆን ለጦር ያስከተተውን ደስ ያሰኝ ዘንድ የሚያስችል አቋም ስለሚሰጠው በብዙ ነገር ከመጠላለፍ ይድናል (2ጢሞ 2፥4)።እስራኤላውያን ከግብጽ እንደ ወጡ ባጋጠማቸው በዚህ በመጀመሪያው ጦርነት እግዚአብሔር ዓላማዬ ነው የሚለው እንዲውለበለብላቸው ነው ያደረገው። እንዲሁ እኛም ከድቅድቅ ጨለማ ወደ ሚደነቅ ብርሃን እንደወጣን በውስጣችን ከፍ ብሎ ሊውለበለብ የሚገባው እግዚአብሔር ዓላማዬ ነው የሚለው ሰንደቅ ነው (ቆላ 1፥13-14)። በሕይወታችን ያሉ ሌሎች ሰንደቆች ሊወርዱና በዚህ ሰንደቅ ሊተኩ ይገባል። ይህ ሰንደቅ ከፍ ብሎ ካልተውለበለበና ካልታየን ከድቅድቅ ጨለማ ወደሚደነቅ ብርሃን ብንወጣም፣ ነገር ግን በጉዞአችን ውስጥ ባሉ የተለያዩ ነገሮች ተሰነካክለን ወደታሰበልን ግብ ከመድረስ እንገታለን።</p><p><br></p>
Piracy-free
Piracy-free
Assured Quality
Assured Quality
Secure Transactions
Secure Transactions
Delivery Options
Please enter pincode to check delivery time.
*COD & Shipping Charges may apply on certain items.
Review final details at checkout.
downArrow

Details


LOOKING TO PLACE A BULK ORDER?CLICK HERE