Life Shaped By Wisdom


LOOKING TO PLACE A BULK ORDER?CLICK HERE

Piracy-free
Piracy-free
Assured Quality
Assured Quality
Secure Transactions
Secure Transactions
Fast Delivery
Fast Delivery
Sustainably Printed
Sustainably Printed
Delivery Options
Please enter pincode to check delivery time.
*COD & Shipping Charges may apply on certain items.
Review final details at checkout.

About The Book

ማንም ጥበብ ቢጎድለው ሳይነቅፍ በልግስና ለሁሉ የሚሰጠውን እግዚአብሔርን ይለምን ለእርሱም ይሰጠዋል (ያዕ 1፥5)የጥበብ ጉድለት ማሰብ የማይገባንን እንድናስብና መኖር የማይገባንን እንድንኖር ያደርገናል። ኑሮን ያለ ጥበብ ለመኖር መሞከር መኪናን ያለ ነዳጅ ለመንዳት እንደመሞከር ነው። አብዛኛውን ጊዜ በኑሮ ውስጥ የሚጎድለን ገንዘብ፣ ጓደኛ፣ ስራ፣ እውቀት፣ ዕድል ይመስለናል። በእርግጥ እነዚህ ነገሮች ሲጎድሉን ቶሎ እናውቃቸዋለን። ጥበብ ሲጎድለን ግን ቶሎ አንነቃም። ይህ ብቻ ሳይሆን የጎደለን ጥበብ መሆኑን ስለማናውቅ ቶሎ ብለን ሌላ ነገር እንደጎደለን እናስባለን። ሰው ገንዘብ ኖሮት ጥበብ ሲጎድለው ገንዘቡ አይበቃውም፤ ጓደኛ ኖሮት ጥበብ ሲጎድለው የብቸኝነት ስሜት ተጠቂ ይሆናል ወይም የተሰጡትን ሰዎች በአነጋገርና በግንኙነት አያያዝ ጉድለት ያጣቸዋል፤ ስራ ኖሮት ጥበብ ሲጎድለው በሚያደርገው ነገርና በውሎው ድካም እንጂ እርካታ አይሰማውም፤ ዕድል ኖሮት ጥበብ ሲጎድለው ችግርና ተራራ እንጂ ደረጃና ተስፋ አይታየውም፤ የሚወደዱ ውጤቶች የማይወደዱ መንገዶች እንዳሏቸው ባለማስተዋል ያለ መንገድ መዳረሻ በመፈለግ ይባክናል። ስለዚህ የጥበብ ጉድለት ያለንን ሁሉ የሌለን ያደርግብናል።በዚህ መጽሐፍ ልዩ ልዩ የጥበብ ገጽታዎችና አሠራሮች እጅግ ሰፊ በሆነ ሁኔታ ተተንትነዋል። ኑሮአችንን በጥበብ እንድንኖር በዚህ መጽሐፍ ይህ እውነት በመጽሐፍ ቅዱሳዊ ንጽጽር ከብዙ ምሳሌዎች ጋር ቀርቧል። በማንበብ ራስዎን ይጥቀሙ፤ ከዚያም ቤተሰብዎንና ቤተክርስትያንን ይጥቀሙ።
downArrow

Details