Saints Era - Volume 1


LOOKING TO PLACE A BULK ORDER?CLICK HERE

Piracy-free
Piracy-free
Assured Quality
Assured Quality
Secure Transactions
Secure Transactions
Fast Delivery
Fast Delivery
Sustainably Printed
Sustainably Printed
Delivery Options
Please enter pincode to check delivery time.
*COD & Shipping Charges may apply on certain items.
Review final details at checkout.

About The Book

የቅዱሳን ዘመን ስንል ምን ማለታችን ነው? በጌታ በኢየሱስ ክርስቶር ሞት ተዋጅተን በትንሣኤው ዳግም የተወለድን ሁላችን፣ አምነን የዳንን አማኞች ብቻ ሳንሆን ቅዱሳን ለመሆን ተጠርተናል (ሮሜ 1፡7 ፥ 1ቆሮ 1፡2)። ቅዱሳን ማለት ለጌታ ለራሱ የተለዩ ገንዘቡ የሆነ ሕዝብ ማለት ነው (ቲቶ 2፡14)። ቅዱሳንነት ጥሪ እንጂ ስም አይደለም። ይህም ጥሪ ለጥቂቶች ብቻ የተሰጠ ሳይሆን፣ በጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅነት ላመኑ ሁሉ የተሰጠ ጥሪ ነው። ቅዱሳን ለመሆን እንደተጠራን የነገረን የእግዚአብሔር ቃል፣ መጠራት ብቻ ሳይሆን በተጠራንበትም መጠራት መመላለስ እንዳለብንም ያሳስበናል (ኤፌ 4፡1)። ስለዚህም ነው ቅዱሳን የሚለው ቃል መጠሪያ ብቻ ያልሆነው። ስለዚህ የቅዱሳን ዘመን ብለን ስንናገር፣ በቅድሚያ፣ ያመንን ሁሉ፣ ቅዱሳን (የተለዩ) ለመሆን ሁላችን እንደተጠራን እውቀቱ እንዲኖረንና በተጨማሪም በተጠራንበት መጠራት መመላለስ ደግሞ ሁላችንእንደሚጠበቅብን ግንዛቤ ውስጥ እንድናስገባም ነው። እነዚህን ሁለት ነገሮች መረዳትና በእነዚህ መረዳቶችም መመላለስ የቅዱሳንን ዘመን ማምጣት ብቻ ሳይሆን፣ የቅዱሳን ዘመን መምጣት አብሳሪዎች እንድንሆንም ያነቃቃል። ይህ የመጀመርያ ቅጽ በሦስት ክፍሎች የተከፈለ ሲሆን፣ የመጀመርያው ክፍል የእግዚአብሔርን ቅዱስነት በተመለከተ የሚናገር ነው። ስለ ቅዱሳን ከመናገራችን በፊት የእግዚአብሔርን ቅዱስነት ማየትና መመልከት አስፈላጊ ነው። በሁለተኛው ክፍል ስለ ቅዱሳን ወይም ስለ ቅዱስ ሕዝብ እንመለከታለን። ቅዱስ የሆነው እግዚአብሔር ነው ቅዱስ ሕዝብ ሊኖረው የሚችለው። እንዲሁም በመጨረሻው ክፍል ላይ በተለያየ ዘመን እግዚአብሔር የተለያየ የሥራ ትኩረት ሊኖረው ስለሚችል አሁን ያለው የሥራ ትኩረት ለማየት ዘመኑን ስለማወቅ እንመለከታለን። ዘመኑን ካላወቅን አሁን ያለንበትን ዘመን የቅዱሳን ዘመን ነው ልንል አንችልም። መልካም ንባብ!
downArrow

Details